Welcome to Lideta Subcity Woreda 8 Administration!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር በሰላም መጡ!       Baga Gara Kutaa Magaalaa Lideta Aanaa 8 Nagaan Dhuftan!

ቁጥራዊ መረጃ

16,000

በወረዳዉ የሚኖር የህዝብ ብዛት

2211

የወረዳዉ ስፋት m2

2441

የወረዳዉ ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ

የዋና ስራ አስፈፃሚዉ መልእክት

የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የአገልግለት ዕለትን ለተገልጋይ ብቻ በማዋል የህዝብ እሮሮን ለመቀነስ ብሎም በተገልጋዮች የሚነሱ አንገብጋቢ የሆኑ ጥያቄዎችን በአግባቡ አድምጦ ለመመለስ በሁሉም ጽህፈት ቤቶች አገልግሎትን በአንድ ማዕከል መስጠት ከጀመረ ጊዜያትን አስቆጥሯል ፡፡

በተለይም በተለያዩ ምክንያቶች ለአሳዛኝ ችግሮች የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በርህራሄ እና በአክብሮት እያዳመጠ ህግና መመሪያ በሚፈቅደው መንገድ ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠትና በመፍታት፤ችግሮችና ቅሬታዎች ወደተነሱበት ተቋማት በቀጥታ ስልክ በመደወልም ጭምር በግልፅ በማነጋገር እልባት እየሰጠ ይገኛል። ይህ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላልና ተገልጋዮቻችን ወደ እኛ ኑ ጥያቄያችሁን አቅርቡ። በእኛ ደረጃ የምንፈታውን ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን ። ከኛ በላይ የሆነውን ለሚመለከተው አካል እናስተላልፋለን። የማንፈታውን ከእናንተ ጋር እንግባባለን። ይህ የ2018 የአገልግሎት አሰጣጥ መርሀችን ነው። .... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ ደረጄ ፈይሳ , የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ
image description

የወረዳዉ አመራሮች

ዜና | Oduu | News
መደበኛ የ10 ቀን ዕቅድ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ተገመገመ!!

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር በ10 ቀናት ንቅናቄ በወረዳ ደረጃ ታቅደው እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች እና አጠቃላይ አመራሩ በተገኙበት ተገምግሟል። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ እንደተናገሩት በቀጣይ አስር ቀናት ስኬታማ ስራዎች መከናወን እንዳለበት አንስተው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የምናረጋግጠው ተጨባጭ የስራ እድል በመፍጠር፣የኑሮ ውድነቱን በማቃለል እና የሌማት ቱርፋት ስራዎችን በማስፋፋት በመሆኑ እቅዶቻችን በመከፋፈል በቅንጅት በመስራት የቀጣይ አስር ቀናት እቅድ አፈፃፀም ለመሳካት ሁሉም በየደረጃው ያለው አመራር መረባረብ ይገባዋል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም አመራሩ የህብረተሰቡን ጥያቄ በሚመልስ ሁኔታ በልዩ ትኩረት በመንግስት ታቅደው እየተተገበሩ ያሉ ተግባሮችን አስተሳስሮ በመስራት የታቀደውን እቅድ ማሳካት እንደሚገባ ተገልጿል።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
መደበኛና ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች በአጠቃላይ አመራር ተገመገመ።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር አጠቃላይ አመራር በተገኘበት መደበኛ እና ወቅታዊ የ10 ቀናት ዕቅድ የንቅናቄ ግባራት፣የስራ እድል ፈጠራ ፣የከተማ ግብርና ተግባር ፀጥታ ያለበት ሁኔታ እና የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ መድረኩን የመሩት የወረዳዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ እንዲፈፀሙ የታቀዱ እያንዳንዳቸው ስራዎቻችንን ተግባራዊ በማድረግና የህዝባችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በጀመርነው የብልፅግና ጉዞ ላይ ተደማሪ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሄድ ዋናው ትኩረታችን ነው በማለት ገልጿል።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በብልጽግና ፓርቲ አሰራር እና አደረጃጀት መመሪያ ዙርያ ለብልፅግና ፓርቲ አባላት ስልጠና ተሰጥቷል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የብልጽግና ፖርቲ አሰራር እና አደረጃጀት ዙርያ ለብልፅግና ፓርቲ ሴት ክንፍ፣ወጣት ክንፍ እና ለመኖሪያ ለአባላት ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው የብልጽግና አሰራርና አደረጃጀት መመሪያ በትክክል መረዳት ለተልዕኮ ስኬታማነት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልፀው የብልፅግና ፓርቲ አሰራርና አደረጃጀትና መመሪያ ፣ የፓርቲው ዓላማና መለያ እሴቶችን፣ ፕሮግራሞችና ፣ የብልፅግና አስራሮች ፣ የፓርቲው ማህበራዊ መሰረት፣ የአባላት መብትና ግዴታዎች በመተግባር ጠንካራ ተቋምና አደረጃጀት መፈጠርና የሚያሰርፁ እንደሆነ ገልፅዋል። መመሪያው ጠንካራ አደራጃጀት እና አባላትን ለማፍራትና ለማብቃት በማስፈለጉ መዘጋጀቱ የተገለጸ ሲሆን በአቅም ግንባታ፣ በአደረጃጀትና በተልእኮ አሰራር መመሪያን አውቆ ተፈፃሚ እንዲሆንና ፓርቲው የሚፈልገውን ቁመናና ቁርጠኝነት እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል::

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በኮሪደር ልማት የተዋበው አዲሱ የልደታ ጎዳናዎችና ፕላዛዎች ገፅታ በከፊል!

በኮሪደር ልማት የተዋበው አዲሱ የልደታ ጎዳናዎችና ፕላዛዎች ገፅታ በከፊል!

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰዉ ሃብት ልማት ጽ/ቤትና ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአገልግሎት ቀንን አስመልክቶ ምልከታ አድርገዋል።

በአስተዳደሩ በሚገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና በጽ/ቤቶች የሚገኙ አመራሩም ሆነ ባለሙያዉ አገልግሎት ፈልጓ የመጣዉን ማህበረሰብ ቅንነት በተሞላበት መንፈስ በማገልገል ላይ መሆናቸዉን በተደረገዉ ምልከታ መታየት ተችሏል ።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለፖሊሶችና ቅጥር ጥበቃዎች በደንብ 148/2016 በቅጥር ጥበቃ መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ሰቷል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የስልጠና ባለሙያ የሆኑት አቶ ታዴ ባዬ ስልጠናውን ሰተዋል። የጽ/ቤቱ ኋላፊ አቶ ዩሀንስ ሰለሞን መመሪያና ደንብን መሠረት በማድረግ ስራዎች እንዲሰሩና ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ስልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ለሴት አመራሮች እና ለቡድን መሪዎች የአመራር ክህሎት ስልጠና ሰጠ።

የአንድን ድርጅት ወይም ተቋም የቆመለትን ዓላማና ራዕይ ወደ ተግባር መለወጥ አሊያም ከግብ ማድረስ እንዲችል ሰዎችንና የአመራር ዘዴዎችን ማቀናጀት ፣የአሰራር ዘዴዎችን መንደፍ፣ሃሳቦችን ማመንጨትና አቅጣጫ ማሳየት ሲችል የስነ-አመራር ተግባር መሆኑ በስልጠናዉ ላይ ተገልጿል ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወርቁ ሴቶች ለተገልጋዮች በቅንነትና በታማኝነት በማገልገል ለሌሎች አርአያ መሆን እንዳለባቸዉና እና መሪነት ለመሆን ያለንን ብቃትና ችሎታ ለማሳየት መታገል መቻል አለብን ሲሉ ተናግረዋል። የወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አይናለም ብርሃኑ መሪነት አርአያ መሆን ነዉ መሪነት ከቤታች የሚጀምረ በመሆኑ ባለንበት ተቋም ላይ አክብሮት በተሞላበት መንፈስ ተገልጋዮችን በማገልገል የመሪነት ብቃታችንን ማሳየት አለብን ሲሉ ተናግረዋል ።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
"ሀገር በቀል እሴቶች ለዘላቂ ሰላም" – ልደታ ወረዳ 08 እና 06 ከወጣቶች ጋር ተወያየ።

ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 እና 06 ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት፣ ወጣቶችን ያሳተፈ "ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል ለትውልድ እሴቶች ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ዙሪያ ሰፊ የውይይት መድረክ ማካሄዱን አስታውቋል። ውይይቱ የተካሄደው ከወረዳው ከተውጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ከሚወክሉ ወጣቶች ጋር ሲሆን፣ የሰላም ባህልን በወጣቱ ዘንድ ለመገንባት አላማ ያነገበ ነው። ውይይቱን የመሩት የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ አበራ እንደተናገሩት፣ ወጣቶች የሀገር ግንባታ ምሰሶ ከመሆናቸው ባሻገር፣ በማኅበረሰብ ውስጥ ሰላምን እና መቻቻልን በማስፈን ረገድ ወሳኝ ሚና አላቸው። አቶ ሄኖክ አክለውም፣ "ሰላም ከውጭ የሚመጣ ሳይሆን በውስጣችን የምንገነባው እሴት ነው። ይህንን ሀገር በቀል የሰላም እና የመቻቻል እሴት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በቅድሚያ እኛ ራሳችን የሰላም አምባሳደር መሆን አለብን። ወረዳው የፀረ-ሰላም ኃይሎችን ተጽዕኖ ለመከላከል የወጣቱን ግንዛቤና ተሳትፎ ለማጠናከር ቁርጠኛ ነው" ብለዋል። የልደታ ወረዳ 08 የሰላምና ጸጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አፈወርቅ ቦጋለ በበኩላቸው፣ የሰላም ማስፈን ሥራ የፖሊስና የጸጥታ አካላት ብቻ ሳይሆን የመላው ኅብረተሰብ በተለይም የንቁ ወጣቶች የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል። አቶ አፈወርቅ እንዳሉት፣ "መቻቻልና ሰላም ሲኖር፣ የሕግ ማስከበር ሥራው ይቀላል። ፖሊስ ወንጀልን ከመከሰቱ በፊት፣ ወጣቶች አለመግባባቶችን በውይይት እንዲፈቱ የማድረግ የሰላም ባህልን ሲያዳብሩ፣ የኅብረተሰብ ደኅንነት ይረጋገጣል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚኒቲ ክፍል ከወጣቶች ጋር ተባብሮ በመሥራት የሰላምን ተቋማዊነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው" በማለት አፅንዖት ሰጥተዋል። በመድረኩ ላይ ወጣቶቹ ሀሳባቸውን በግልጽ በማንሳት፣ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

image
image
image

አቅጣጫ ጠቋሚ

በወረዳዉ ህንፃ ዉስጥ ያሉ ፅህፈት ቤቶች አቅጣጫ ጠቋሚ

ግራውንድ ፍሎር የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት

አንደኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ንግድ ጽ/ቤት

ገቢዎች ጽ/ቤት

ሁለተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ስራና ክህሎት ጽ/ቤት

ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት

የህፃናት ማቆያ ዴይኬር

ሶስተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ፐብሊክ ሰርቪና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት

ፓርቲ ጽ/ቤት

አራተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ጽ/ቤት

ምክር ቤት

ከተማ ግብርና ጽ/ቤት

ትምህርት ጽ/ቤት

አምስተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት

ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት

ህብረት ስራ ጽ/ቤት

ወጣትና ስፓርት ጽ/ቤት

ስድስተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ፋይናንስጽ/ቤት

ፅዳትና ከተማ ውበት ጽ/ቤት

ቤተመጽሀፍት

ሰባተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ዋና ስራ አስፈፃሚ

ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት

ያግኙን | Contact Us

Phone: +251913152882