ዜና | Oduu | News
መደበኛ የ10 ቀን ዕቅድ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ተገመገመ!!

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር በ10 ቀናት ንቅናቄ በወረዳ ደረጃ ታቅደው እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች እና አጠቃላይ አመራሩ በተገኙበት ተገምግሟል። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ እንደተናገሩት በቀጣይ አስር ቀናት ስኬታማ ስራዎች መከናወን እንዳለበት አንስተው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የምናረጋግጠው ተጨባጭ የስራ እድል በመፍጠር፣የኑሮ ውድነቱን በማቃለል እና የሌማት ቱርፋት ስራዎችን በማስፋፋት በመሆኑ እቅዶቻችን በመከፋፈል በቅንጅት በመስራት የቀጣይ አስር ቀናት እቅድ አፈፃፀም ለመሳካት ሁሉም በየደረጃው ያለው አመራር መረባረብ ይገባዋል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም አመራሩ የህብረተሰቡን ጥያቄ በሚመልስ ሁኔታ በልዩ ትኩረት በመንግስት ታቅደው እየተተገበሩ ያሉ ተግባሮችን አስተሳስሮ በመስራት የታቀደውን እቅድ ማሳካት እንደሚገባ ተገልጿል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
መደበኛና ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች በአጠቃላይ አመራር ተገመገመ።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር አጠቃላይ አመራር በተገኘበት መደበኛ እና ወቅታዊ የ10 ቀናት ዕቅድ የንቅናቄ ግባራት፣የስራ እድል ፈጠራ ፣የከተማ ግብርና ተግባር ፀጥታ ያለበት ሁኔታ እና የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ መድረኩን የመሩት የወረዳዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ እንዲፈፀሙ የታቀዱ እያንዳንዳቸው ስራዎቻችንን ተግባራዊ በማድረግና የህዝባችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በጀመርነው የብልፅግና ጉዞ ላይ ተደማሪ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሄድ ዋናው ትኩረታችን ነው በማለት ገልጿል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በብልጽግና ፓርቲ አሰራር እና አደረጃጀት መመሪያ ዙርያ ለብልፅግና ፓርቲ አባላት ስልጠና ተሰጥቷል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የብልጽግና ፖርቲ አሰራር እና አደረጃጀት ዙርያ ለብልፅግና ፓርቲ ሴት ክንፍ፣ወጣት ክንፍ እና ለመኖሪያ ለአባላት ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው የብልጽግና አሰራርና አደረጃጀት መመሪያ በትክክል መረዳት ለተልዕኮ ስኬታማነት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልፀው የብልፅግና ፓርቲ አሰራርና አደረጃጀትና መመሪያ ፣ የፓርቲው ዓላማና መለያ እሴቶችን፣ ፕሮግራሞችና ፣ የብልፅግና አስራሮች ፣ የፓርቲው ማህበራዊ መሰረት፣ የአባላት መብትና ግዴታዎች በመተግባር ጠንካራ ተቋምና አደረጃጀት መፈጠርና የሚያሰርፁ እንደሆነ ገልፅዋል። መመሪያው ጠንካራ አደራጃጀት እና አባላትን ለማፍራትና ለማብቃት በማስፈለጉ መዘጋጀቱ የተገለጸ ሲሆን በአቅም ግንባታ፣ በአደረጃጀትና በተልእኮ አሰራር መመሪያን አውቆ ተፈፃሚ እንዲሆንና ፓርቲው የሚፈልገውን ቁመናና ቁርጠኝነት እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል::

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በኮሪደር ልማት የተዋበው አዲሱ የልደታ ጎዳናዎችና ፕላዛዎች ገፅታ በከፊል!

በኮሪደር ልማት የተዋበው አዲሱ የልደታ ጎዳናዎችና ፕላዛዎች ገፅታ በከፊል!

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰዉ ሃብት ልማት ጽ/ቤትና ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአገልግሎት ቀንን አስመልክቶ ምልከታ አድርገዋል።

በአስተዳደሩ በሚገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና በጽ/ቤቶች የሚገኙ አመራሩም ሆነ ባለሙያዉ አገልግሎት ፈልጓ የመጣዉን ማህበረሰብ ቅንነት በተሞላበት መንፈስ በማገልገል ላይ መሆናቸዉን በተደረገዉ ምልከታ መታየት ተችሏል ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለፖሊሶችና ቅጥር ጥበቃዎች በደንብ 148/2016 በቅጥር ጥበቃ መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ሰቷል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የስልጠና ባለሙያ የሆኑት አቶ ታዴ ባዬ ስልጠናውን ሰተዋል። የጽ/ቤቱ ኋላፊ አቶ ዩሀንስ ሰለሞን መመሪያና ደንብን መሠረት በማድረግ ስራዎች እንዲሰሩና ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ስልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ለሴት አመራሮች እና ለቡድን መሪዎች የአመራር ክህሎት ስልጠና ሰጠ።

የአንድን ድርጅት ወይም ተቋም የቆመለትን ዓላማና ራዕይ ወደ ተግባር መለወጥ አሊያም ከግብ ማድረስ እንዲችል ሰዎችንና የአመራር ዘዴዎችን ማቀናጀት ፣የአሰራር ዘዴዎችን መንደፍ፣ሃሳቦችን ማመንጨትና አቅጣጫ ማሳየት ሲችል የስነ-አመራር ተግባር መሆኑ በስልጠናዉ ላይ ተገልጿል ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወርቁ ሴቶች ለተገልጋዮች በቅንነትና በታማኝነት በማገልገል ለሌሎች አርአያ መሆን እንዳለባቸዉና እና መሪነት ለመሆን ያለንን ብቃትና ችሎታ ለማሳየት መታገል መቻል አለብን ሲሉ ተናግረዋል። የወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አይናለም ብርሃኑ መሪነት አርአያ መሆን ነዉ መሪነት ከቤታች የሚጀምረ በመሆኑ ባለንበት ተቋም ላይ አክብሮት በተሞላበት መንፈስ ተገልጋዮችን በማገልገል የመሪነት ብቃታችንን ማሳየት አለብን ሲሉ ተናግረዋል ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
"ሀገር በቀል እሴቶች ለዘላቂ ሰላም" – ልደታ ወረዳ 08 እና 06 ከወጣቶች ጋር ተወያየ።

ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 እና 06 ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት፣ ወጣቶችን ያሳተፈ "ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል ለትውልድ እሴቶች ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ዙሪያ ሰፊ የውይይት መድረክ ማካሄዱን አስታውቋል። ውይይቱ የተካሄደው ከወረዳው ከተውጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ከሚወክሉ ወጣቶች ጋር ሲሆን፣ የሰላም ባህልን በወጣቱ ዘንድ ለመገንባት አላማ ያነገበ ነው። ውይይቱን የመሩት የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ አበራ እንደተናገሩት፣ ወጣቶች የሀገር ግንባታ ምሰሶ ከመሆናቸው ባሻገር፣ በማኅበረሰብ ውስጥ ሰላምን እና መቻቻልን በማስፈን ረገድ ወሳኝ ሚና አላቸው። አቶ ሄኖክ አክለውም፣ "ሰላም ከውጭ የሚመጣ ሳይሆን በውስጣችን የምንገነባው እሴት ነው። ይህንን ሀገር በቀል የሰላም እና የመቻቻል እሴት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በቅድሚያ እኛ ራሳችን የሰላም አምባሳደር መሆን አለብን። ወረዳው የፀረ-ሰላም ኃይሎችን ተጽዕኖ ለመከላከል የወጣቱን ግንዛቤና ተሳትፎ ለማጠናከር ቁርጠኛ ነው" ብለዋል። የልደታ ወረዳ 08 የሰላምና ጸጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አፈወርቅ ቦጋለ በበኩላቸው፣ የሰላም ማስፈን ሥራ የፖሊስና የጸጥታ አካላት ብቻ ሳይሆን የመላው ኅብረተሰብ በተለይም የንቁ ወጣቶች የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል። አቶ አፈወርቅ እንዳሉት፣ "መቻቻልና ሰላም ሲኖር፣ የሕግ ማስከበር ሥራው ይቀላል። ፖሊስ ወንጀልን ከመከሰቱ በፊት፣ ወጣቶች አለመግባባቶችን በውይይት እንዲፈቱ የማድረግ የሰላም ባህልን ሲያዳብሩ፣ የኅብረተሰብ ደኅንነት ይረጋገጣል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚኒቲ ክፍል ከወጣቶች ጋር ተባብሮ በመሥራት የሰላምን ተቋማዊነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው" በማለት አፅንዖት ሰጥተዋል። በመድረኩ ላይ ወጣቶቹ ሀሳባቸውን በግልጽ በማንሳት፣ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ፐብሊክ ሰርቪስ የሰዉ ሃብት ልማት ጽ/ቤት፣ምክር ቤትና ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአገልግሎት ቀንን አስመልክቶ ምልከታ አድርገዋል።

በአስተዳደሩ በሚገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና በጽ/ቤቶች የሚገኙ አመራሩም ሆነ ባለሙያዉ አገልግሎት ፈልጎ የመጣዉን ማህበረሰብ ቅንነት በተሞላበት መንፈስ በማገልገል ላይ መሆናቸዉን በተደረገዉ ምልከታ መታየት ተችሏል ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የብሎክ ካውንስል ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፡፡

በጉባኤው ላይ የብሎክ ካውንስል ተጠሪዎች ሰራተኞችና አመራሮች ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ እንደተናገሩት አስተዳደሩ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶችን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ አውስተው፣ ከአስተዳደሩ ጥረት ጎን ለጎን ሕብረተረሰቡ በአካባቢው በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ልማትን ከማፋጠን ባሻገር በመንግሥትና በሕብረተሰቡ መካከል ያለውን በጋራ የመሥራት ባሕል እንደሚያጠናክር አመላክተዋል፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ሰለሞን በበኩላቸው የሕብረተሰቡን የልማት ፍላጎት የማሟላት ሥራ በመንግሥት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን በህዝቡ ተሳትፎ ሊታገዝ እንደሚገባው ገልጸው በሕብረተሰብ ተሳትፎ በተከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ የብሎክ ካውንስል አደረጃጀቶች በሀብት ማሰባሰብ፣ በግንባታ ሥራዎች አፈጻጸም፣ በአካባቢ ጽዳት፣ በሰላምና ጸጥታ ስራዎችና በሌሎች ተግባራት ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸው፣ አሁንም የሕብረተሰብ ተሳትፎ ሥራዎችን በማጠናከር ክፍተቶችን በማስተካከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የጉባኤው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በተያዘው በጀት ዓመት በሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸው፤ በቀጣይም ተሳትፏቸውን በማሳደግ በርካታ የልማት ስራዎችን ከመንግሥት ጋር በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ለስራ ፈላጊ ወጣቶችና ሴቶች የልል ክህሎት ስልጠና ተሰጠ።

በስልጠናው ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር ይትባረክ ብርሃነ ሰልጣኞች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት በስራ ላይ ማድረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ እና ስራቸውን በእውቀት እንዲሰሩ ማድረግ ውጤታማነታቸው ላይ ያለው አስተዋፆ ከፍተኛ በመሆኑ ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል ይገባቸዋል ብለዋል ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚረዳም ገልጸዋል። የወረዳው ም/ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የክቴ የማታው ስልጠናው ለስራ ውጤታማነት አቅም የሚፈጥርና የሚያግዝ መሆኑና እንዲሁም በሚመርጡት የስራ ዘርፍ ስራውን በእውቀት እንዲሰሩ ከማገዝ አኳያ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውና በቀጣይም ስልጠናውን ወደ ተግባር መቀየር እንዳለባቸው በአፅንኦት ገልፀዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጸጥታ አካል እና የሰላም ሰራዊት አባላት የምስጋና እና የዕውቅና መርሐ-ግብር ተካሄደ።

በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 አስተዳደር የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጸጥታ መዋቅር አባላትና ለሰላም ሰራዊት አባላት የምስጋና ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የወረዳው የጸጥታ መዋቅር አባላትና የሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል። የልደታ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍታለሁ ከፍያለሁ በመልዕክታቸው ሰላምን ለማረጋገጥ የከተማ እና የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ፣የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ፣ደንብ ማስከበር፣ የወረዳው የፀጥታና የሰላም ሰራዊቱ አባላት ፣ ወጣቶች ፣ፎሌዎች የማይተካ ሚና በመጫዎት የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ በማለት በቀጣይ ጊዜም ከተለያዩ የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት የከተማውን የክፍለ ከተማውን የወረዳውን ሰላምና ጸጥታ ከምን ግዜም በላይ ሳያሳስበን በታላላቅ ሐገራዊ ፕሮጀክቶች በልማቱ ብቻ ምናተኩርበት አመት እና የኢትዮጵያዊን የከፍታን የምናረጋግጥበት እና ቀጣይ ሐገራዊ ምርጫ በአሸናፊነት የምናጠናቀቅበት ይሆናል በማለት ለተሳታፊዎች በፓርቲና እና በራሳቸው ስም አመስግነዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ የመሰቀል ደመራና እሬቻ በዓል መጠናቀቅን አስመልክቶ ነዋሪው እና የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ከምንጊዜውም በላይ ላደረገው አስተዋፅኦ ምስጋናቸው ላቅ ያለ እንደሆነ ገልፀዋል። በስተመጨረሻም በተለያየ መንገድ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የሰርተፍኬት እውቅና እና ምስጋና ተካሂዷል እንደዚህ አይነት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተገልፀዋል። መስከረም 29/2018 ዓ.ም

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ለመገንባት የሚያስችል የመልሶ ማደራጀትና የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸዉን በሱፐርቪዥን ቡድን ምልከታ ተደርጓል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተቋቋመ የሱፐርቪዥን ቡድን በልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤትና በወረዳ 1,4 እና 06 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በመገኘት ሲያካሂድ የቆየውን ሱፐርቪዥን በዛሬው ዕለት በማጠናቀቅ ግብረ መልስ ሰጥቷል። በበጀት አመቱ ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ለመገንባት እና የገዥ ትርክት ግንባታን የሚያረጋግጡ የፖለቲካና የአደረጃጀት ዕቅዶች ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ለዚህ መሳካት የሚያስችሉ የመልሶ ማደራጀት እና የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸዉ ይታወቃል። ተግባሩ የተመራበትን አግባብና የተገኙ መልካም ልምዶችን ለማስፋት እና አልቆ ለመፈፀም ክፍተቶችን ለማረም ዓላማ ያደረገ የሱፐርቪዥን ቡድን የፖለቲካና አደረጃጀት ስራዎችን በክፍለ ከተማ፤ በወረዳ፤ በህብረት እና ቤተሰብ ምልከታ አድርጓል። ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ለመገንባት የሚያስችል የመልሶ ማደራጀትና የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸዉ በግብረ መልስ የተመላከተ ሲሆን በአፈፃፀም ሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ግንባታ ግብ ስኬት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል። #prosperiry_lideta_branch. #በአዲስ_እይታ_የልደታ_ከፍታ #ጠንካራ_ፓርቲ_ለጠንካራ_መንግስት

image
image
image
image