image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ጽዳትና ዉበት አስተዳደር ጽ/ቤት በክረምት የተተከሉ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ እንክብካቤ አደረገ።

ጥቅምት 14, 2017
የወረዳ 08 ጽዳትና ውበት አስተዳደር በክረምት ወራት የተተከሉ አረንጓዴ አሻራ ችግኞች ጽድቀትና ዕድገት እንዲረጋገጥ የተጠናከረ የእንክብካቤ ሥራዎችን አከናውኗል ። የልደታ ክፍለ ከተማ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የክቴ የማታዉ ጌዶ ዋሻ እንደክፍለ ከተማ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በርካታ ችግኞች የተተከለበት ቦታ በመሆኑ እነዚህ ችግኞችን ሁሉም ተቋማት በየዘርፉ በመንከባከብ የአረንጓዴ አሻራ ሽፋንን በማሳደግ ከተማችንን ዉብ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ​የወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ፈይሳ ችግኞች ልክ እንደ ህጻናት ስለሆኑ ከተተከሉበት ዕለት ጀምሮ ችግኞቹ ጤናማ ሆኖ እንዲያድጉ እና ከተባይ እንዲሁም ከእንስሳት ከብቶች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ገልፀዉ ችግኞቹ ለቀጣይ ትውልድ የሚተርፍ አረንጓዴ አካባቢን እንዲፈጥሩና የወረዳችንን ገጽታ እንዲያላብሱ የዕለት ተዕለት ክትትልና እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። ​የወረዳው ጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስቻለዉ ምህረቱ እንደገለጹትችግኝ መትከል ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ባለፉት የክረምት ወራት የተተከሉትን ችግኞች ለማሳደግ ልዩ ትኩረት በማድረግ የጥንቃቄ እና የእንክብካቤ ሥራዎች የወረዳውን የለመለመ ገጽታ ከማጎልበት ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች