image
image
image
image
image

ሰንደቅ ዓላማችን ለብሄራዊ መግባባት እና አንድነታችን!!

ጥቅምት 4, 2017
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ምክር ቤት 19ኛዉ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በማስመልከት የፌዴራል ፖሊስ ፣የአዲስ አበባ ፖሊሰ፣የምክር ቤት አባላት እና የወረዳዉ ሰራተኞች በተገኙበት የሁነት መድረክ አካሂዷል ። ​በዕለቱ የተዘጋጀው መርሃ ግብር የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ በማንሳት፣ የባንዲራውን ከፍ ያለ ታሪካዊ እና ብሔራዊ ፋይዳ በሚያስታውሱ ሁነቶች ቀረቧል። የወረዳ 08 ክብርት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኑሪያ ኢብራሂም ሰንደቅ ዓላማ የህዝቦች አብሮነት፣ የሉዓላዊነት እና የነጻነት መገለጫ እንደሆነ ገልጸዋል። ሰንደቅ ዓላማን ማክበር እና ከፍ ማድረግ የዕለት ተዕለት የዜግነት ግዴታ መሆኑን ገልፀው አባቶች አደራ ሰጥተው ያቆዩትን ሰንደቅ ዓላማ በላብ፣ በዕውቀት እና በጠንካራ ስራ ከፍ አድርጎ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል። በመጨረሻም ክብርት አፈ ጉባኤዋ ለተሳታፊዎቹ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን አስወግዶ፣ኢትዮዊነታችን በልማትና በዲሞክራሲ ጎዳና ዉስጥ የህዝቦችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ፣በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከበለፀጉ ሀገሮች ተርታ ትሰለፍ ዘንድ የጀመርነዉን የለዉጥ ጉዞ ወደ ማይቀለበስ ደረጃ ለማድረስ በአንድነትና በጋራ ስሜት አብሮ በመቆም በዓመቱ በመንግስት ትኩረት አግኝተዉ የታቀዱ ልማቶችን ስራዎችንና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዕቅዶቻችንን ለማሳካት በሀገራችን ሰንደቅ አላማ ቃል አስገብተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች