image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠር ምቹ፣ ማራኪ እንዲሁም ውብና ጽዱ የመኖሪያ መንደር ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ታህሳስ 19, 2017
የህብረተሰቡን አኗኗር ዘይቤ እየቀየሩ፤ እያዘመኑ የሚገኙ የተቀናጀ ሞዴል የብሎክ ስራ በልደታ ክ/ከተማ ውስጥ ብሎኮችን የማዘመን ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በክፍለ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡን በማስተባበር ‎ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠር ፅዱ፣ ምቹና ውብ እንዲሁም ማራኪ አካባቢን መፍጠር ያስፈልጋል በማለት አስተዳደርሩ ሰንቆ በተነስው ተግባር በሁሉም ወረዳዎች እና ብሎኮች ተግባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል። "በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ" እቅድ አንዱ ግብ የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ መፍጠር ሲሆን ምቹና ውብ እንዲሁም ማራኪ አካባቢ እንዲፈጠር ከነዋሪው ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ይገኛል። በተፈጠረው የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ የክ/ከተማው ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለኑሮ ምቹና ተስማሚ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ ብሎኮቹን በማልማት፣ በማፅዳት፣ በማስዋብ የተለያዩ ተግባራት እያከናወኑ ይገኛል፡፡ አስተዳደሩ ሞዴል ብሎኮችን አጠናክሮ በማስቀጠል ሌሎች ተጨማሪ ምቹ ብሎኮችን በመፍጠር አካባቢያቸውን ምቹ፣ ውብና ጽዱ እና ማራኪ መኖሪያ መንደር ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል። እየተከናወኑ ከሚገኙት የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ተግባራት መካከል በጽዳት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በከተማ ግብርና፣ በሰላምና ፀጥታ፣ ECD፣ በውስጥ ለውስጥ መብራት፣ የመሳሰሉት ስራዎች ተካተውበታል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች