image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ምክር ቤት 13 ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤዉን አካሂዷል ።

ሰኔ 6, 2017
የወረዳ 08 ምክር ቤት ክብርት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኑሪያ ኢብራሂም በንግግግ መክፈቻቸዉ በ2018 በጀት ዓመት በረካታ ድሎችን ያስመዘገበበት ዓመት ነዉ ።በ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የምክር ቤቱ አባላት ከጅምሩ እስከ መጨረሻው በንቃት በመሳተፍ እንደ ወረዳና እንደ ክፍለከተማችን ዉጤቱ ያማራ መሆኑን ገልፀዋል። በበጀት ዓመቱ በተደረገዉ ክትትልና ድጋፍ አብዛኛዉ ተቋማት ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገቡበት በጀት ዓመት መሆኑን ገልፀዉ እንደ ምክር ቤት የተሰሩ ስራዎች በዋናነት በከተማ ግብርና ሰራዎች ፣በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች፣በሰዉ ተኮር ስራዎች የማዕድ ማጋራት እና የቤት እድሳት ፣የልማት ስራዎች ከፍተኛ ስራ በምክር ቤቱ መሰራቱን ክብርት አፈ ጉባኤዎ ገልፀዋል ።። የወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ፈይሳ በበጀት ዓመቱ በ9ወር የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት አቅርበዉ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ፣የልማትና የሰዉ ተኮር ስራዎች፣በሰላምና ፀጥታ ጉዳይ፣የትምህርት ጥራትን ማሳደግ፣የኢኒሸቲቪ ስራዎች፣በስራ ዕድል ፈጠራ፣በህገ- ወጥ ስራዎች ፣የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት በቅዳሜና እሁድ ገበያ ምርቶች መቅረባቸዉ እና የህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ በዋናነት ተጠቃሽ ናቸዉ በዚህም መሰረት በዚህ በጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸዉን በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ተገልጿል ። አገልግሎት አሰጣጥን ግልፀና ቀልጣፍ ለማድረግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የዲጂታል አገልግሎትን በማዳበር የህዝባችንን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የተገልጋይንና የባለሙያ እርካታን በማሳደግ ወረዳችንን ከፍ ማድረግ ያሰፈልጋል ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ገልፀዋል። ለ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ እና ለነበሩት የልማት ስራዎች ላይ የወረዳዉ ነዋሪና የምክር ቤት አባላት ለነበራቸዉ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዉ ለተጀመሩ የልማት ስራዎችና የጂ +4 ግንባታን ለማጠናቀቅ ድጋፋችሁ አይለየን ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል። በበጀት ዓመቱ በርካት የልማት ስራዎች፣የኢኒሸቲቫ ስራዎች እና የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት በቅዳሜና እሁድ ገበያ ምርቶች መቅረባቸዉ ለነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እነዚ ተግባራቶች ችግር ፈች ናቸዉ ሲሉ ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል ። የምክር ቤት አባላቱ የ2ኛ በደበኛ ጉባኤዉን ቃላ ጉበኤ አፅድቆ ወ/ሮ ዮዲት አርሴሞን የወረዳ 08 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አድርጎ ሾሟል። በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የሚመለከታቸዉ የጽ/ቤት ኃላፊዎችና ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች